ዓመታዊው “ጆብ ፌር -2019 ኤክስፖ” ተካሄደ

Posted by:Anonymous (not verified)

ዓመታዊው “ጆብ ፌር- 2019 ኤክስፖ” ሃምሌ 18/2011 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማዕከል ተካሂዷል፡፡ ኤክስፖው በ2011 ዓ.ም ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የተመረቁ አዳዲስ ምሩቃን ሥራ ፈላጊዎችን ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር የማገናኘት ዓላማ ያለው መሆኑን አዘጋጆቹ የደረጃ አካዳሚ የሥራ ኃላፊዎች ገልፀዋል፡፡

ደረጃ አካዳሚ ለአዳዲስ ምሩቃን መሰረታዊ የቅድመ ሥራ ስልጠና “ሶፍት ስኪል ትሬይኒንግ“ የሚያመቻች ተቋም መሆኑን እና በየዓመቱ ሰልጣኝ ምሩቃን በማብቃት ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚህ ዓመታዊ ጆብ ፌር ላይ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፤ የሃገር ውስጥ እና ዓለም ዓቀፍ ቀጣሪ ድርጅቶች እንዲሁም ሥራ ፈላጊ ምሩቃን የተገኙ ሲሆን ከዝግጅቶ ጎን ለጎንም በጉዳዩ ላይ ያተኮረ የግማሽ ቀን ኮንፍረንስ ተካሂዷል፡፡