“ሚዲያ ኤክስፖ-2019” ሊካሄድ ነው፡፡

Posted by:Mariawit
21 January 0

በኦን ፕሮሞሽን ኃላ/የተ.የግል ማህ. የተዘጋጀውና በሃገራችን የሚዲያ ዘርፍ የመጀመሪያ ሁነት የሆነው “ሚዲያ ኤክስፖ-2019” በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከጥር 17-19/2011 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

በኤክስፖው በቴሌቪዥን ፣በሬዲዮ፣በህትመትና ዲጀታል ሚዲያ ስራ ላይ የተሰማሩ ከ70 በላይ የሚዲያ ተቋማት እና ሌሎች ከሚዲያ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስራዎችን የሚያከናውኑ ድርጅቶች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡  የሚዲያ ኤክስፖው ዓላማ በሚዲያ ተቋማት መካከል የእርስበእርስ ትስስር በመፍጠር የልምድ ልውውጥ ማድረግ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቀቅ የገበያ ዕድሎችን ማስፋት መሆኑን ኤክስፖ ዳይሬክተሩ አቶ ቴዎፍሎስ መኮንን ገልፀዋል፡፡

ቀጣዩን የሚዲያ ኤክስፖ ከሃገር ውስጥ ተሳታፊዎች በተጨማሪ የውጭ ሀገር የሚዲያ ተቋማትን በማሳተፍ በስፋት ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ መጀመሩን ኤክስፖ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የሚዲያ ኤክስፖ-2019 ጎብኚዎችም በነፃ መጎብኘት እንደሚችሉም ለማወቅ ተችሏል፡፡