የዒድ ኤክስፖ በድምቀት ተከፈተ፡፡

Posted by:Anonymous (not verified)
23 May 0

በየዓመቱ ታላቁ የሮመዳን ፆምን ተከትሎ የሚዘጋጀው ታላቁ ኢድ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በድምቀት ተከፈተ፡፡

ከግንቦት 15 እስከ ግንቦት 26 ቀን 2011ዓ.ም ድረስ የሚቆየው ይህ ኤክስፖ ዘንድሮ ሲዘጋጅ ለ8ኛ ጊዜ መሆኑን እና በኤክስፖውም የሃገር ውስጥና ከውጭ ሃገር የመጡ ተሳታፊዎች ምርትና አገልግሎታቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘው የቀረቡ መሆናቸውንና ከኤክስፖው ጎን ለጎን ሰብዓዊ ድጋፍን የተመለከቱ ሌሎች ተግባራትም እንደሚከናወኑ በመክፈቻው ሥነ-ስርዓት ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡

በሌላም በኩል ዝግጅቱ በሚካሄድባቸውም ቀናት ለልጆች ልዩ የመዝናኛ ቦታ የተዘጋጀ ከመሆኑም ባሻገር የዳይኖሰር ትዕይንትም በክፍያ እንደሚቀርብ ከአዘጋጁ ሃላል ፕሮሞሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለመረዳት ተችሏል ፡፡