9ኛው ከተማ ዓቀፍ የቴክኒክና ሙያ የንቅናቄ ሳምንት ተጀመረ፡፡

Posted by:Anonymous (not verified)
07 March 0

“ለኢንዱስትሪ ዕድገታችን ቴክኒክና ሙያ የመጀመሪያ ምርጫችን! ”በሚል መሪቃል የተዘጋጀውና ከየካቲት 27-መጋቢት 1/2011 ዓ.ም ድረስ የሚቆየው የቴክኒክና ሙያ የንቅናቄ ሳምንት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በድምቀት ተከፍቷል፡፡

በመክፈቻው ስነ ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሰለሞን ክፍሌ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ፤የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለኢንዱስትሪው ሽግግር ስኬት የሚጫወቱትን ሚና ለማሳደግ ይህን መሰል ዝግጅት መካሄዱ ጠቀሜታው የጎላ ነው ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት ያላቸውን ዕምነት ገልፀዋል፡፡

በሌላም በኩል የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሃላፊው የተከበሩ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የዚህ ዝግጅት ዓላማ ቴክኒክና ሙያን በማጠናከር ችግር ፈቺ ትውልድ ማፍራት መሆኑን እና ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ተስማሚ ቴክኖሎጂን በመቅዳት የኢንዱስትሪውን ሽግግር ማፋጠን እንደሚችሉ ለማስገንዘብ ጭምር መሆኑን በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም በኤግዚቢሽኑ ላይ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለዕይታ ያቀረቡ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ከመንግስትና ከግል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛዎች ፤ ከ30 በላይ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እና አጋር አካላት የተሳተፉ ሲሆን ኤግዚቢሽኑ ለጎብኚዎችም ያለ ክፍያ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡