ማዕከሉ የበጎ አድራጎት ተግባራትን አከናወነ፡፡

Posted by:admin

ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ዘንድሮ በታቀደ መልኩ የክረምት ስራዎች አካል የሆኑትን የበጎ አድራጎት ተግባራት ሰኔ 16/2011 ዓ.ም የማዕከሉ ሰራተኞች፣ በማዕከሉ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ማህበራት አባላት እና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በችግኝ ተከላ፣ በአካባቢ ፅዳትና ለችግረኛ ተማሪዎች ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እና ለአቅመ ደካማ አረጋውያን የብርድ ልብስ ድጋፍ በማድረግ አከናውኗል፡፡

የበጎ አድራጎት ድጋፉን በተመለከተ በሁለት ምዕራፍ የተከፈለ እንደሆነ እና የዚህ ምዕራፍ ተግባራት በዛሬው ዕለት በዝግጅቱ ላይ ለተገኙ የብሔራዊ አጸደ ህፃናትና 1ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ያካተተ ለ100 የት/ቤቱ ችግረኛ ተማሪዎች ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም በአካባቢው ለሚገኙ 40 አቅመ ደካሞችና አረጋውያን የብርድ ልብስ ድጋፍ ለማድረግ ታቅዶ መሰራቱን፤ በቀጣዩ ምዕራፍም በዓመቱ መጨረሻ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ ለችግረኛ አረጋውያን የበዓል መዋያ የቅርጫ ስጋ ድጋፍ እንደሚደረግ እና ዩኒፎርምን ጨምሮ ሙሉ የትምህርት ድጋፍ በዛሬው ዕለት ላልተገኙ ለቀሪዎቹ የት/ቤቱ ተማሪዎች ለማስረከብ ዝጅግት በመደረግ ላይ መሆኑን አቶ ታምራት አድማሱ የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ገልፀዋል፤ ድጋፉን የበለጠ በማጠናከር ማዕከሉ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እንደሚወጣም አረጋግጠዋል፡፡

በመጨረሻም ዋና ሥራ አስኪያጁ ይህንን የበጎ አድጎራት ተግባር በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላደረጉ የወረዳው የአካባቢ ልማትና ፀጥታ ኮሚቴ አባላት እና ለመላው የማዕከሉ ሰራተኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡