ሀበሻ -የፋሲካ ኤክስፖ በኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፈተ፡፡

Posted by:Mariawit
09 April 0

ከመጋቢት 27-ሚያዚያ 19/2011 ዓም ድረስ ለ23 ተከታታይ ቀናት የሚቆየው እና ከ500 ሺህ በላይ ህዝብ ይጎበኘዋል ተብሎ የሚጠበቀው ሀበሻ -የፋሲካ ኤክስፖ በኤግዚቢሽን ማዕከል በድምቀት ተከፍቷል፡፡

በዝግጅቱ ላይ 500 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር አምራቾችና ሌሎች ድርጅቶች ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ይዘው የቀረቡ መሆኑን ፣ በምርቶቹ ላይም የ30 በመቶ ቅናሽ እንደሚደረግ እና በየቀኑም በአንጋፋና ወጣት ድምጻውያን የሙዚቃ ኮንሰርት ፣ልዩ ልዩ የመዝናኛ ዝግጅቶች ፣ ዕለታዊ ሽልማቶች የተዘጋጁ መሆኑን እና በሃገራችን የመጀመሪያ የሆነው የዳይኖሰር ትዕይንትም በድጋሚ ለጎብኚዎች ክፍት መደረጉን የአዘጋጁ ሀበሻ ዊክሊ ኃላ.የተ.የግ.ማህ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አዶኒክ ወርቁ በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ አስታውቀዋል፡፡

በዚህ ደማቅ የፋሲካ ኤክስፖ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ባህል ቱሪዝምና ስነ-ጥበብ ቢሮ ሃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር አቶ ነብዩ ባዬ የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም አዘጋጁ ሀበሻ ዊክሊ ኃላ.የተ.የግ.ማህ ለዚህ ኤክስፖ መሳካት ትብብር ላደረጉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ የሚዲያ ተቋማት ፣ የጸጥታ አካላት በተለይም ለአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት የላቀ ምስጋና በማቅረብ ዝግጅቱ በይፋ ተከፍቷል፡፡